የአልኮል ምርቶች ከቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ባለፈ በማህበራዊ ሚዲያዎችም ማስተዋወቅ ሊከለከል ነው‼️
የአልኮል ምርቶችን በማህበራዊ ሚዲያዎች ማስተዋወቅን በከፊል የሚከለክል የህግ ረቂቅ መሰናዳቱም ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለሰልጣን የአልኮል ምርቶችን በማህበራዊ ሚዲያዎች ማስተዋወቅን በከፊል የሚከለክል የህግ ረቂቅ ተሰናድቶ በሒደት ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል።
ኢትዮጵያ ከዓመታት በፊት የአልኮል ምርቶችን እንደ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ባሉ መገናኛ ብዙኃን ማስተዋወቅ በህግ ማገዷ ይታወቃል።
የአልኮል አምራች ተቋማት በአሁን ሰዓት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም፤ ምርታቸውን እያስተዋቁ እና ለበርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች እየደረሱ ነው ተብሏል።
ከእነዚህ መካከልም የማህበራዊ ሚዲያ በብዛትና በተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እየተጠቀሙ እንደሆነ ተነግሯል።
ይህንን እየተስፋፋ የመጣውን በማህበራዊ ሚዲያ የአልኮል ማስታወቂያን በተቻለ መጠን ለመገደብ ታስቦ፤ የህግ ማዕቀፍ ተሰናድቶ በሒደት ላይ እንደሚኝ በኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን የህግ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ ፍሬሰላም ዮሴፍ ተናግረዋል ።
በኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን የተሰናዳው ረቂቅ ህግ ወደ ጤና ሚኒስቴር መላኩንም ስራ አስፈፃሚዋ ጨምረው ተናግረዋል።
====================