Sew Meseretu — Ephrem Tamiru
ሰው መሠረቱ መቼ ይለያያል
በአንድ አምሳል ተፈጥሮ አንድ ሆኖ ይታያል
ሃብትን የታደላት ትልቅ ሰው ይባላል
ያጣም ድህነቱን አምኖ ይቀበላል
ያለለትን ሊኖር እድሜውን ሲገፋ
ከቶ በህይወቱ ማነው የማይለፋ
ደስታና መከራ ማግኘቱ ማጣቱ
ሁሉም በየተራ አይቀርም መምጣቱ
ተፈራርቆ የሚኖር በየራሱ ጊዜ
በየራሱ ጊዜ
የአንድ ቦይ ውሃ ነው ተድላና ትካዜ
ተድላና ትካዜ
ውጣ ውረድ ባለው የህይወት መሰላል
የህይወት መሰላል
የዚህች ዓለም ነገር በዚህ ይመሰላል
በዚህ ይመሰላል
————————-
የሆነለት ወጥቶ ያቃተውም ወርዶ
ሁሉም ይቀበላል የኑሮን ተፈርዶ
ህይወት በደረጃ ሰው ይነጣጥላል
አንዱን ላይ አድርጎ አንዱን ታች ይጥላል
የሌለው ዳቦ አጥቶ ያለው ሙክት ሲያንሰው
ያለው ሙክት ሲያንሰው
ላገኘው ሲጨምር ካጣ እየቀነሰው
ካጣ እየቀነሰው
የእድሜ መጨረሻ ሲመጣ ሰዓቱ
ሲመጣ ሰዓቱ
ሞቱ ግን አንድ ናት ቢለይም ህይወቱ
ቢለይም ህይወቱ
——————————
ሊቁ ዘመን እንጂ አይደለም ጠቢብ
የሚሆን ምን አለ እንደ ሰው ሃሳብ
በዓለም ላይ ጊዜ ነው ሁሉን የሚያደርገው
ተስካሩን ያወጣል ሰውስ በሰረገው
የበላይ በበታች ይገፋል ከወንበር
ይገፋል ከወንበር
በዓለም ምን ይኖራል ወትሮስ እንደነበር
ወትሮስ እንደነበር
ተማሪ ቆሞለት ይበላል ደብተራ
ይበላል ደብተራ
ትልቅ ሲወድቅ ነው የትንሾች ተራ
የትንሾች ተራ
የበላይ በበታች ይገፋል ከወንበር
ይገፋል ከወንበር
በዓለም ምን ይኖራል ወትሮስ እንደነበር
ወትሮስ እንደነበር
ተማሪ ቆሞለት ይበላል ደብተራ
ይበላል ደብተራ
ትልቅ ሲወድቅ ነው የትንሾች ተራ
የትንሾች ተራ
ተማሪ ቆሞለት ይበላል ደብተራ
ይበላል ደብተራ
ትልቅ ሲወድቅ ነው የትንሾች ተራ
የትንሾች ተራ