Postlar filtri


የትግራይ ብሔርተኛ ትህነግ እና የኤርትራ ብሔርተኞች ድል ያደረጉት ከ30 አመታት በላይ ታግለው ነው፤ በእነዚህ አመታት ህዝባዊ ቅቡልነት እንዲኖራቸው ሰርተዋል! ይህን እንዳሳኩ ለድል በቅተዋል።

እኛስ?
ፋኖ ቅርፅ ከመያዙ በፊት ህዝባዊ ቅቡልነት አግኝቷል፤ የአገዛዙን መዋቅር በማፍረስ ትግሉን እንደሚደግፍ በተግባር አሳይቷል!! ቀጣዩ ምዕራፍ ለስልጣን መብቃት ነበር። ያ ሲሆን እያየን አይደለም!! እኔ መሪ ልሁን እኔ መሪ ልሁን በማለት የነበረውን ወርቃማ ዕድል አባከኑት!!
ቀኑ ሲገፋ ችግሮች ይደራረባሉ!!


የአብይ አህመድ ቡድን!
የአብይ አህመድ ቡድን ምርጫ ያካሂዳል፡፡ የተወሰኑ ወንበሮችን ለአጋሮቹ ይለቅና በከፍተኛ ድምጽ ማሸነፉን ያውጃል፡፡ ምርጫውን ተከትሎ እሱን በሚጠቅም መልኩ የህገ መንግስት ማሻሻያ ያካሂዳል፡፡ የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ተካተዋል እንዲባል አንዳንድ የአማራ ህዝብ ወሳኝ ጥያቄዎች ያልሆኑ እንደ ሰንደቅአላማ ያሉ ጉዳዮችም ይሻሻላሉ፡፡ በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሞ ብሄርተኞች ተጨማሪ ጉዳዮችን  ያካትታሉ፤ ኦሮምኛ ቋንቋን የስራ ቋንቋ ያደርጋሉ ወዘተ። የኮሪደር ልማቱና ሌላው የህዝብን ቀልብ ሊገዛ የሚችል ብልጭልጭ፣ ግን ደግሞ የተወሰነ ቡድንን የሚያከብር “ልማት” ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ አብይ የአረንጓዴ ልማት አርበኛ ተብሎ እንዲሸለም ሎቢ ይደረጋል፡፡ ገንዘብ ተከፍሎም ሆነ በሌላ መንገድ ሽልማቱም ይመጣል፡፡ "ህዝቡ ነፃነት ተሰጥቶት ነፃነትን ማስተዳደር አልቻለም” ተብሎ የአብይን ቡድን አሜን ብሎ እንዲቀበል ይደረጋል…

የፋኖ ትግል አሁን በተያዘው የእውር-ድንብር መንገድ የሚቀጥል ከሆነ በራሱ በፋኖው ድክመትና በዲያስፖራው መጋለብ ምክንያት ይሽመደመዳል፡፡ ግሽበት ክሽፈትን ይወልዳል፡፡ የተወሰነው የፋኖ ታጋይ እጁን ይሰጣል፡፡ የሚታሰረው ይታሰራል፤ ፍርፋፊ የሚሰጠው ይሰጠዋል፡፡ የተወሰነው ይሰደዳል፡፡ የተወሰነው እያንገራገረ በጫካዎች ውስጥ ይንቀሳቀሳል፡፡ የሚያመጣው ጠብ የሚል ለውጥ ግን አይኖርም፡፡ ከፋኖው ትግል መዳከም ጋር ተያይዞ አብዛኛው አክቲቪስት ነኝ ባይም ጥጉን ይይዛል፡፡

በዚህ ሂደት በአማራ ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥና ቁዘማ ይነግሳል፡፡ ብዙዎች ራሳቸውን ከፖለቲካ ያገላሉ፡፡ ብዙዎች ጥቅመኛ የሆነ የአካባቢ ወይም የሃይማኖት ፖለቲካ ሊያራምዱ ይችላሉ፡፡ “የአማራ ብሄርተኝነት አይድንም፤ የአማራ ፖለቲካ አልቆለታል” ብሎ ተስፋ የሚቆርጠው ነፋስ አመጣሽም ብዙ ነው፡፡ ለውድቀቱ ሁሉም ተጠያቂነት ያለበት ቢሆንም መካሰሱ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ሁሉም ራሱን ከተጠያቂነት ለማዳን ሌሎችን መክሰሱን ይቀጥልበታል፡፡ መካሰሱና መጠፋፋቱ በሌላ መልክ ይቀጥላል፡፡

ለማንኛውም የአማራ ህዝብ መከራ መራዘሙ እርግጥ ነው፡፡ ይህም በጠላት አቅም ሳይሆን በእኛው በራሳችን ውድቀት ምክንያት የመጣ ነው፡፡ ዋነኛው ውድቀታችን በኤሊት ደረጃ ስር ከሰደደው የእውቀት ድህነት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የእውቀት ድህነት የወለደው እልህ፣ መጠፋፋት፣ ጥቅመኝነትና ህዝበኝነት የትግሉ ነቀርሳ ነው፡፡
የብሄርተኝነት ምንነትና ኃያልነት የገባቸው ጀግኖች ግን ጸንተው በትግላቸው ይቀጥላሉ፡፡ የፋኖ ትግል የአማራ ብሄርተኝነት አንዱ ገጽታ እንጂ የአማራ ብሄርተኝነትን እንደማይተካ የሚገነዘቡ ብሄርተኞች ጸንተው ይቀጥላሉ፡፡ ዛሬ በነፋስ አመጣሽ ተውጠው የሚሰቃዩት ጽኑዎቹ የአማራ ብሄርተኞች ይበልጥ ይጠናከራሉ እንጂ አይዳከሙም፡፡ የፖለቲካን ተቀያያሪ ባህሪ ስለሚገነዘቡ ደቅድቅ ጨለማ የመሰለው የዛሬው ሁኔታ በትግል እንደሚቀየር ይረዳሉ፡፡ ስለሆነም ከቶም ተስፋ አይቆርጡም፡፡ የእስካሁኑን ሂደት ገምግመው አዳዲስ የጥናት መጽሔቶችን (ጆርናሎችን) ይፈጠራሉ፡፡ አዳዲስ ሲቪክ ማህበራትን ይገነባሉ፡፡ አዳዲስ የአማራ ተቋማትን ያብባሉ፡፡ አሁን ያሉትና በአረም የተዋጡት ተቋማት እንዲጠሩና እንዲታረሙ ይደረጋል፡፡ የማይድነው ተፈጥሯዊ ሞቱን ይሞታል፡፡ መሞቱም ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም፡፡
በአለም ታሪክ “ሞቢሊላይዝድ” ሆኖ እንደገና የከሰመ ብሄርተኝነት የለም፡፡ ስለሆነም የአማራ ብሄርተኝነት በየጊዜው ከሚገጥሙት ፈተናዎች እየተማረ በትውልዶች ቅብብል እያደገና እየጎመራ ይሄዳል እንጂ አይሞትም፡፡ ስለሆነም ይህን ሃቅና መጪውን የጭቆና ዘመን የተገነዘቡ የአማራ ልጆች ከወዲሁ ቦታ ቦታቸውን መያዝ አለባቸው፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪ መመረቂያ ጽሁፋቸውን በአማራ ታሪክ እና በአማራ ብሄርተኝነት ላይ ማድረግ አለባቸው፡፡ በአማራ ጥናት ዙሪያ በታወቁ መጽሄቶች ላይ ማሳተም ይጠበቅባቸዋል፡፡ አመታዊ የአማራ ጥናት ጉባኤዎችን በየአሁጉሩ ማካሄድ ይገባቸዋል፡፡ በብሄርተኞች የሚመሩ አዳዲስ የጥናትና ምርምር፣ የሰብአዊ መብት፣ የሎቢ፣ የባህል እና የፖለቲካ ተቋማትን ማቋቋም ያስፈልጋል፡፡

የኤርትራ ብሄርተኞች ለድል የበቁት ከ30 አመት በላይ ታግለው መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ አልቆለታል ተብሎ ሞቱ የታወጀው ኦነግም በሌላ መልክ ለድል የበቃው ከ40 አመት በኋላ መሆኑን መረዳት ይገባል፡፡ አይሪሾች እንዴትና ለስንት ዘመን ታግለው ለድል እንደበቁ፤ እስራኤሎች እንዴትና ለስንት ዘመን ታግለው ለድል እንደበቁ፤ ፍልስጤማዊን ተስፋ ሳይቆርጡ ለ75 አመታት እየታገሉ እንደሚገኙ የሚገዘቡ የአማራ ብሄርተኞች በትግላቸው ጽንተው ይቀጥላሉ፡፡ ድልም ያደርጋሉ!

የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!!!

(ጽሁፉን ከአመት በኋላ አብረን እንገመግመዋለን)

April 07/2025 የተለጠፈ


የአማራ ህዝብ ልጆቹን ቆንጥጦ ወደ አንድ እንዲመጡ ማድረግ ይችል ነበር፤ ይህ እንዳይሆን እንቅፋት የሆነው ተማርኩ የሚለው መንጋ ነው!! የተማረ መንጋ ደግሞ እጅግር የለውም!! ከዚህ መውጣት ካልተቻለ (የሚቻል አይመስልም) ታሪካዊ ስህተት ይሰራል!! ያሉን ጠላቶች ከመብዛታቸው የተነሳ በአንድ ቁመንም ቢሆን ተገዳዳሪ ናቸው፤ ከተከፈልን ግን ሽንፈት እጣ ፈንታችን ይሆናል!! አሁን ሀብት በማጋበስ ላይ ያለ ፋኖ ነኝ እያል የሚጋልብህን ነቅቻለሁ በለው!! ወንድሙን መስደብ ትቶ ነፃ እንዲያወጣህ ጠይቀው!!

የዝምታ ጊዜው አልቋል!!

በዚህም አለን 👇
https://www.facebook.com/share/p/18fgvpVu7M/




ካሊጉላ አብይ ያባከነው የሀገር ሀብት
የጫካ ፕሮጀክት  1,500,000,000,000
አዲስ አበባ ኮሪደር ልማት (phase 1) 100,000,000,000
መተሐራ ሪዞርት 30,000,000,000
አድዋ መታሰቢያ 20,000,000,000
ሳይንስ ሙዚየም 10,000,000,000
ቤተመንግሥት ዕድሳት 10,000,000,000
ጨበራ ጨርጨራ ፖርክ 10,000,000,000
አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል 10,000,000,000
እንጦጦ ፓርክ 6,000,000,000
አንድነት ፓርክ 5,000,000,000
ጎርጎራ 4,000,000,000
ወንጪ 4,000,000,000
የወዳጅነት ፓርክ 4,000,000,000
መስቀል አደባባይ ፓርክ 4,000,000,000
የአ/አ ከተማ ከንቲባ ቢሮ እድሳት 2,000,000,000

Total: 1.79 T

3.4k 0 15 12 36

I remain silent for undetermined period.


ነባራዊ ሁኔታን አይቶ የራስ የግምገማ ውጤት ላይ መድረስ ብልህነት ነው! የሆነ አካል በሚለቀው ፕሮፖጋንዳ መላጋት መንጋነት ነው!! እኔ በግሌ የአማራ ህዝብ ሰቆቃ በኛ ዘመን እንዲያበቃ የምችለውን ሁሉ እያደረኩ ነው!! ሀሳቤን ስንሰጥ ሁሌም ከቀናነት ነው!!!


በግለሰብ ውሳኔ (ውሳኔው ማጣራትን የሚፈልግ ቢሆንም) ድርጅትን ካለፈርስኩ የምትል መንጋ አድብ! በአገዛዙ ክላሲካል አትደንስ!! ተደራጀው የሚለው አካል እስቲ ሌላውን መሳደብ ትቶ የሚሰሩ ስራዎች ላይ ያተኩር! እኛም እንደግፈው!


ወንድምክን አጣብቂኝ ውስጥ ከተህ አማራጭ አሳጥተህ እጅ የመስጠት ውሳኔ ሲደርስ ከአገዛዙ ጋር በአንድ ዜማ ማዜም ወይ ሁኔታው አለመረዳት ነው። አልያም የአማራን ህዝብ ትግል ለማክሸፍ መስራት ነው!


መንጋው አሁንም ሽምጥ እየተጋለበ ነው!! ሲነቃ በገደል እየተንከባለለ ያገኘዋል!! ነገ ብየ ነበር ባልል ደስ ይለኝ ነበር!!! አሁን ለአማራ ብሎ የታገለውን ወንድምህን አራክስ፣ ባንዳው ተለየ፣ ጠራ ገለመኔ እያልክ አጣጥል!

መንጋው፣ መንጋ ጋላቢውና ብልፅግና አንድ አይነት ዜማና ዜና ላይ ናቸው!


የሳሙኤል እና የአስቻለው በለጠ (2ቱም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ሀይል ሴንተራል ኮማንድ አባል ናቸው) ጦር እርስ በእርሱ ሊገጥም ነው ማለት ነው?🤔

ጎበዝ ዝም ተብሎ የሚታይ አይደለም!
1ኛ) ሰርጎ ገብ እንዳንለው በመዋቅር ነው እያታዘዙ ያሉት።
2ኛ) የሀሰት ወሬ ነው እንዳንል አመራሮቹ ስለጉዳዩ በግልፅ እያወሩ ነው!

በአንድ ሴንትራል ኮማንድ ስር ነኝ የሚል አካል እንዴት እንደዚህ አይነት ነገር ያደርጋል?
ከሁለቱ አንዱ #የግድ እውነት ነው? አስቻለው ወይም ሳሙኤል አንዳቸው ለጠላት የሚሰሩ ባንዳ ናቸው? ይህ ካልሆነም ለትግሉ የማይመጥኑ የሰፈር አለቃ ናቸው ማለት ነው?

እንደዚህ አይነቱን ሸፋፍነን አናልፈውም!! የግድ መጥራት አለበት!👇
https://vm.tiktok.com/ZMSNojn8D/


1=
በቀጣይ ሒደቶች የሚገመገም ይሆናል!




ፋኖ ሌባ አይደለም፡፡ ሌባም ፋኖ ሊሆን አይችልም፡፡ ፋኖ ዘራፊ አይደለም፡፡ ዘራፊም ፋኖ ሊሆን አይችልም፡፡ ፋኖ ትምህርት ጠል አይደለም፡፡ ትምህርት ጠልም ፋኖ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለሆነም ፋኖ መምህራንን ገደለ፣ ፋኖ ትምህርት ከለከለ የሚለው ዘገባ ፋኖን አይመለከተውም፡፡ ፋኖ ለአማራ ህዝብ እየታገለ እንዴት አማራን የሚያጎሳቁል ተግባር ሊፈፅም ይችላል?

መምህራንን የሚያሰቃይና የሚገድል፣ ትምህርትን የሚከለክል፣ ህዝብን የሚያማርር እሱ ፋኖ አይደለም፡፡ በስሙ መጠራት ይገባዋል፡፡ ፀረ ህዝብ ነው፡፡ ፀረ ስልጣኔ ነው፡፡ ኋላቀር ነው፡፡

ብልፅግና የራሱን ሌባና ዘራፊ አደራጅቶ እንደሚያሰማራ አያከራክርም፡፡ ይህን ማንኛውም ከነፃነት ታጋይ ጋር የገጠመ አምባገነን የሚያደርገው ነው፡፡ እነዚህ ብልፅግና ያሰማራቸው ሰዎች ግን በትክክለኛው ስማቸው መጠራት ይገባቸዋል፡፡ ክቡር የሆነውን የፋኖን ስም እንዲጠቀሙ መፍቀድ የለብንም፡፡ “ሌባ ፋኖ፣ ዘራፊ ፋኖ፣ የብልፅግና ፋኖ፣ የብአዴን ፋኖ…” የሚል አገላለፅ ያላዋቂ አገላለፅ ነው፡፡ ፋኖ ከሆነ ሌባ ሊሆን አይችልምና፡፡ ሌባ ከሆነም ፋኖ ሊሆን አይችልምና፡፡ ፋኖ ሌባ አይደም ማለት ግን ወደ ሌብነት ሊዘቅጥ አይችልም ማለት አይደለም፡፡ ፋኖ ሽፍታ አይደለም ማለት ወደ ሽፍታነት ሊዘቅጥ አይችልም ማለት አይደለም፡፡ የፋኖ አርበኝነት በተማሩ የአማራ ልጆች በተደራጀና በአማራ ብሄርተኝነት ርእዮት በሚመራ የፖለቲካ ሃይል እስካልተመራ ድረስ በጊዜ ሂደት ሊዘቅጥ የሚችልበት እድል ሰፊ ነው፡፡ በጠራ ብሄርተኛ ርእዮትና በጠንካራ ድርጅት ካልተመራ እንደ ጎፈሬያም ያረጀ አምበሳ አለ ሲሉት ሞቶ ሊገኝ የሚችልበት ሰፊ ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ፋኖ ወደዚህ ደረጃ አልዘቀጠም፡፡ ስለሆነም የአማራን ህዝብ በሚያጎሳቁል እውቀት ጠል ተግባር ላይ ሊሰማራ አይችልም፡፡

ስለዚህ ፋኖዎች እንዲህ አይነቱን ፀረ ህዝብ ተግባር አለማድረጋቸው ብቻ ከተጠያቂነት እንደማያድናቸው አውቀው ድርጊቱን አጥብቀው ማውግዝ አለባቸው፡፡ የፋኖ የህዝብ ግንኙነትና ፕሮፓጋንዳ ድክመት ትግሉን እየጎተተው ነው፡፡ ፋኖ ከሚታገለው ጠላት የበለጠ የህዝብ ግንኙነትና ፕሮፓጋንዳ አቅም መገንባት ይኖርበታል፡፡ ካልሆነ አጥቂ ሳይሆን ተከላካይ እየሆነ ይቀጥላል፡፡ ክቡር የሆነው ስሙም ይጠፋል፡፡ ፋኖ ብዙ የሚያኮሩ እሴቶች እያሉት ራሱን መሸጥ አልቻለም፡፡

ፀረ ህዝብነትና ፋኖነት የማይገናኙ ተቃራኒ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ይህን በተግባርና በትርክት ደረጃ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!!!


አሸናፊ ማህበረሰባዊ ንቅናቄ ቁጣን መፍጠር መቻል አለበት፡፡ የተፈጠረው ቁጣናና የቁጭት መንፈስ ግለቱን ጠብቆ እንዲቀጥል ማደረግ መቻልም ይኖርበታል፡፡ መጠኑ ይለያይ እንጂ በየትኛውም ጊዜና ሁኔታ በማንኛውም ህብረተሰብ ውስጥ ቁጣን ሊፈጥሩ የሚችሉ ጉዳዮች አሉ፡፡ እንደ አማራ ባሉ ህዝቦች ውስጥ ደግሞ በደሉና ግፉ ሞልቶ እየፈሰሰ ነው፡፡ በአማራ ህዝብ ላይ ከ80 አመታት በላይ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ የመጣ ከፍተኛ ግፍና በደል አለ፡፡ ይሁን እንጅ በደል መኖሩ ብቻውን ግን ታጋይ ማህበረሰብን አይፈጥርም፡፡ ግፍ መኖሩ በራሱ ትግልን አይጋብዝም፡፡ ከፍተኛ ቁጣን ሊፈጥር የሚችል ህዝባዊ በደል ቁጣን ሳይፈጥር ሊያልፍ የሚችልበት እድል በጣም ሰፊ ነው፡፡

ቁጣ የሚፈጠረውና ግለቱን ጠብቆ የሚቀጥለው በደሉን ህዝባዊ ንቅናቄ በሚፈጥር አኳኋን የሚቀምር የሃሳብ አንድነት ያለውና የተደራጀ ልሂቅ ሲኖር ነው፡፡ ይህን ጠንካራ ሃይል ባለመፍጠራችን በየጊዜው በህዝባችን ላይ የሚፈፀሙት ግፎች እንደዘበት ተረስተው እየቀሩ ነው፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ፣ በመጽሄት፣ በመጽሐፍ አይጻፉም፡፡ አይሰነዱም፡፡ በተለያዩ ቋንቋዎችና ሚዲያዎች ሪፖርት አይደረጉም፡፡ ለተወሰኑ ቀናት ጩኸት ይስተጋባና ሁኔታው ተረሳስቶ ይቀራል፡፡ የሚካሄዱት የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎችም ያልተቀናጁ ከመሆናቸውም በላይ ወረተኛ ናቸው፡፡ የተፈናቀሉ ወገኖች ጉዳይ ይረሳል፡፡ የተገደሉ ወገኖች ጉዳይ ይረሳል፡፡ የታሰሩ ወገኖች ጉዳይ ይዘነጋል፡፡ በትግል ሂደት ዋጋ የከፈሉ ወገኖች በሚረሰቡት ጊዜ ደግሞ እነሱም ሆኑ ሌላው ወገን ከትግሉ ይሸሻል፡፡ የገጠመን ችግር ይህን ነው!

እስኪ “የአብይ ቡድን በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ካወጀበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ ቦታ ይህን ያህል አማሮች ተገደሉ” እያለ የሚመዘግብ አለ? ስንት የድሮን ጥቃት እንደተፈፀመና ስንት ንፁሃን ወገኖቻችን እንደተጨፈጨፉ መዝግቦ የሚይዝ አለ? መስዋእትነት የከፈሉ ጀግኖችን ስም ዝርዝር ለቅሞ የሚይዝ አለ? በሀገሪቱ በየቦታው ታጉረው ግፍ ስለተፈፀመባቸውና አሁንም ስለሚሰቃዩት የአማራ ልጆች የጠራ መረጃ ያለው አለ? እስካሁን ስንት ሪፖርቶች በተለያዩ ቋንቋዎች ወጡ? ስንት ዘገባዎች በአለም አቀፍ ጋዜጣዎች ታተሙ? ስንት መጽሃፎች ለህትመት በቁ?

ይህ የውድቀት አካሄድ የግድ መቀየር አለበት፡፡ በህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ያልተቋረጠ ግፍ እያንዳንዷን ክስተት ለቅመን በመያዝ ቁጭትና ቁጣን በሚፈጥር መልኩ መጠቀም ይኖርብናል፡፡ ጠላት አጀንዳችን ሊያስጥለን ሲሞክር “እምቢ!” ብለን ነክሰን መያዝ አለብን፡፡
ቁልፉ ግን ሁልጊዜም መደራጀት ነው፡፡ ቁልፉ ከትግሉ ሂደት (ከድክመቱም ከጥንካሬውም ትምህርት እየቀሰሙ) ሁልጊዜም መሰባሰብ ነው፡፡ የህዝብ በድል ለብሄርተኝነት ፍግ ነው፡፡ ያፋፋዋል፡፡ ነገር ግን ብሄርተኝነቱ ፍግ አንሶት እንዳይቀነጭር ወይም ፍጉ በዝቶበት እንዳይጋሽብ በጠንካራ አደረጃጀቶች መመራት አለበት፡፡ አማራ ያለው ትልቁ መሳሪያው ብሄርተኝነቱ ነው፡፡ ስለሆነም ብሄርተኝነቱን የነፋስ አመጣሽ አረም እንዳይውጠው ሁልጊዜም መኮትኮት ይገባል፡፡ ብሄርተኝነቱ ከየትኛውም ሃይማኖት ጋር ጋብቻ ሳይፈፅም ሴኩላርነቱን ጠብቆ እንዲቀጥል እና ፍትሃዊነቱን ጠብቆ እንዲያድግ መኮትኮት ያስፈልጋል፡፡ ብሄርተኝነቱን “እኔ እኔ” ከሚሉ ፖፕሊስቶች ነቅቶ መጠበቅም አስፈላጊ ነው፡፡

“የአማራ ህዝብ ዋናው ሀብቱ ብሄርተኝነቱ ነው” የሚለውን ሃቅ ያልተገነዘበ ታጋይ ነኝ ባይ ትግል አልገባውም!

የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!!!


እዚህ ላይ ተደርሷል፤ ይታያል!!


እንኳን አደረሳችሁ የሚል ሚኒስትር መ/ቤት መቋቋም ያለበት ይመስለኛል!!!


እናርጅ እናውጋ!
በአማራ ክልል እናርጅ እናውጋ ውስጥ በአብይ ቡድን የተፈፀመው ጭፍጨፋ የሚነግረን በጣም ብዙ ነገር አለ፡፡ ዋናው መልእክት የንፁሃኑ ጭፍጨፋ መጪውን እጅግ አስከፊ ዘመን የሚያሳይ መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ በላይ ጭፍጨፋና ከዚህ በላይ ግፍ እየመጣ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ንፁሃንን ጨፍጭፈው “ፅንፈኛ ተደመሰሰ” እንደሚሉ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ንፁሃንን አግተው የታገተ ሰው እየለም እያሉ እንደሚክዱ፣ አማሮችን በገፍ አስረው ግፍ እየፈፀሙ ግፍ የተፈፀመበትና የሚፈፀምበት ሰው የለም እያሉ እንደሚናገሩ፣ ይህንን ፕሮፓጋንዳቸውን ደግሞ ህዝብ እስኪሰለች በማቅረብ ለማሳመን እንደሚሞክሩ የሚያሳይ ነው፡፡

የቡድኑ መመሪያ ዳንኤል ክብረት በአፋሪካ አመራር አካዳሚ የብልፅግናን ካድሬዎች ሰብስቦ ሲያሰለጥን የተናገረው ነው፡፡ “በዚህ ድህረ እውነት አለም ማሸነፍ የሚቻለው አንድን ጉዳይ ደግሞና ደጋግሞ በተቀናጀ ሁኔታ በማቅረብ ነው፡፡ አንድን ጉዳይ ዳጋግመን ስናቀርበው ህዝቡ ‹አሁንስ በዛ!› ካለ ገብቶታል ዓላማችንም ተሳክቷል ማለት ነው” ብሎ ነበር፡፡ የብልፅግና የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ይህ ነው፡፡ የአብይ ቡድን ብርቱካን በተባለች እህታችን ላይ ያደረገውን እርብርብ እና የእኛን ምላሽና ሽንፈት ልብ ይሏል፡፡ እንደ መሳይ መኮነን ያሉ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ያልገባቸው ሰዎች “አሁንስ አበዛችሁት! አሁንስ እጅ እጅ አላችሁ!” እያሉ ሲጽፉ ስናይ የነዳንኤል ክብረት ስትራቴጂ ምን ያህል እንደሰራ እንገነዘባለን፡፡ መሳይ መኮነንን በስም ጠቀስነው እንጅ ሁላችንም ከዚያ የተሻለ ስራ አልሰራንም፡፡ አጀንዳውን ሙጭጭ ብለን መያዝ ሲገባን አስረክበን ቤታችን ገብተናል፡፡ በዚህም ምክንያት ቀጣይ ብዙ አማራ ቢያልቅና ብንዘግበው ያንንም አጀንዳ ውሸት ነው ብሎ እንደሚያስጥለን የሚያሳይ ነው፡፡ አሳፋሪ አክቲቪዝም!
የአብይ ቡድን ስራውን እየሰራ ነው፡፡ መጪው ጭፍጨፋ ከእናርጅ እናውጋ እየበለጠ እንደሚሄድ መጠራጠር አይገባም፡፡ የጅምላ እስሩና ስቃዩ፣ ስደቱ፣ አንገት መድፋቱ ሁሉ እየመጣ ነው፡፡ ይህን እጅግ አስቀያሚ ሁኔታ መቀልበስ ግን ይቻላል፡፡ የችግሩም ሆነ የመፍትሄው ምንጮች ደግሞ እኛው ነን፡፡ ሌላ ቦታ ማንጋጠጥ አይገባም፡፡
መፍትሄው በየእለቱ የሚጠቃው ህዝባችን ጥቃትና ውርደት ተሰምቶን ለህዝባችን ስንል፣ ከእርስ በእስር መጠፋፋት፣ ከእርስ በእስር ጥላቻ፣ ከቂምና ከበቀል መራቅ እና “ያለፈው አለፈ” ብሎ መተባበር ብቻ ነው፡፡ መፍትሄው “እኔ ብቻ ነኝ ትክክል፣ የእኔ መንገድ ብቻ ነው ትክክሉ” ከሚል ከንቱና ፍሬ ቢስ አስተሳሰብ እርቆ ለህዝብ ህልውናና ጥቅም ሲባል መተባበር ነው፡፡ መፍትሄው ለጋራ አሸናፊነት ሲባል መሸነፍ ነው፡፡ መፍትሄው ራስን ከከፋፋይ አክቲቪስት ማራቅ ነው፡፡ መፍትሄው ራስን፣ ትግሉንና የጠላትን ሁኔታ በየጊዜው መገምገምና ሁኔታው የሚጠይቀውን ስትራቴጂ መቅረጽ ነው፡፡ መፍትሄው በእቅድ መመራት ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ዋናውና ቁልፉ መፍትሄ በአማራ ብሄርተኝነት ርእዮት መመራት ነው፡፡
ከንቱዎች እንደሚሉትና እንደሚመስላቸው ከትግሉ ሜዳ እስክንድር ነጋ ባይኖር ወይም ሌሎች ከንቱዎች እንደሚመስላቸው ዘመነ ካሴ ቢወጣ የሚመጣ አንዳችም ለውጥ የለም፡፡ የአማራ ትግል ችግር ከእነዚህ ግለሰቦች በላይ በመሆኑ የእነዚህ ግለሰቦች መኖር አለመኖር ጋር ሊያያዝ አይችልም፡፡ ስለሆነም ከግለሰቦች ራስ ወርዶ (ከማሞገስና ከማኮሰስ ተቆጥቦ) በድርጅት ግንባታ ላይ ማተኮር ነው፡፡ እንደ ህዝብ የእኛ ትልቁና ቋሚው ድክመታችን የድርጅት ግንባታ ችግር ነው፡፡ ይህን ፈተና ሳናልፍ የምናመጣው አንዳችም ለውጥ የለም፡፡ ስለሆነም ከዋናው ጠላት በላይ ግለሰቦችን ዋነኛ ኢላማ በማድረግ ጎራ ለይቶ መጠፋፋቱ የጋራ ውድቀትን ካልሆነ በስተቀር የሚያስገኘው አንዳችም ውጤት የለምና ከዚህ የጥፋት ጎዳና መውጣት ይጠበቅብናል፡፡ ኋላቀርነት ይብቃ! ከጠላት ይልቅ በጠላት ላይ መጨከን ይብቃ!

ይህ ሳይሆን ቀርቶ የፋኖ ትግል አሁን ባለበት የእውር-ድንበር ጎዳና የሚቀጥል ከሆነ ግን እንኳን ህዝብን ነፃ ሊያወጣ የራሱንም ህልውና መጠበቅ አይችልም፡፡ ከመንቦጅቦጅ ወጥቶ የሰከነ የትግል ምህዋር ውስጥ መግባት ግዴታ ነው፡፡

የወገኖቻችንን መስዋእትነት ወደ ሞት እንዳንቀይረው እንጠንቀቅ!

ለገባንበት መቀመቅ ዋነኛዎቹ ተጠያቂዎች እኛው ራሳችን መሆናችንን እንቀበል!

አማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!!!


ሻለቃ መንበሩ ተሰዋ ነው የምትሉኝ!? 😭


😖

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.
OSZAR »