እናርጅ እናውጋ!
በአማራ ክልል እናርጅ እናውጋ ውስጥ በአብይ ቡድን የተፈፀመው ጭፍጨፋ የሚነግረን በጣም ብዙ ነገር አለ፡፡ ዋናው መልእክት የንፁሃኑ ጭፍጨፋ መጪውን እጅግ አስከፊ ዘመን የሚያሳይ መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ በላይ ጭፍጨፋና ከዚህ በላይ ግፍ እየመጣ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ንፁሃንን ጨፍጭፈው “ፅንፈኛ ተደመሰሰ” እንደሚሉ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ንፁሃንን አግተው የታገተ ሰው እየለም እያሉ እንደሚክዱ፣ አማሮችን በገፍ አስረው ግፍ እየፈፀሙ ግፍ የተፈፀመበትና የሚፈፀምበት ሰው የለም እያሉ እንደሚናገሩ፣ ይህንን ፕሮፓጋንዳቸውን ደግሞ ህዝብ እስኪሰለች በማቅረብ ለማሳመን እንደሚሞክሩ የሚያሳይ ነው፡፡
የቡድኑ መመሪያ ዳንኤል ክብረት በአፋሪካ አመራር አካዳሚ የብልፅግናን ካድሬዎች ሰብስቦ ሲያሰለጥን የተናገረው ነው፡፡ “በዚህ ድህረ እውነት አለም ማሸነፍ የሚቻለው አንድን ጉዳይ ደግሞና ደጋግሞ በተቀናጀ ሁኔታ በማቅረብ ነው፡፡ አንድን ጉዳይ ዳጋግመን ስናቀርበው ህዝቡ ‹አሁንስ በዛ!› ካለ ገብቶታል ዓላማችንም ተሳክቷል ማለት ነው” ብሎ ነበር፡፡ የብልፅግና የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ይህ ነው፡፡ የአብይ ቡድን ብርቱካን በተባለች እህታችን ላይ ያደረገውን እርብርብ እና የእኛን ምላሽና ሽንፈት ልብ ይሏል፡፡ እንደ መሳይ መኮነን ያሉ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ያልገባቸው ሰዎች “አሁንስ አበዛችሁት! አሁንስ እጅ እጅ አላችሁ!” እያሉ ሲጽፉ ስናይ የነዳንኤል ክብረት ስትራቴጂ ምን ያህል እንደሰራ እንገነዘባለን፡፡ መሳይ መኮነንን በስም ጠቀስነው እንጅ ሁላችንም ከዚያ የተሻለ ስራ አልሰራንም፡፡ አጀንዳውን ሙጭጭ ብለን መያዝ ሲገባን አስረክበን ቤታችን ገብተናል፡፡ በዚህም ምክንያት ቀጣይ ብዙ አማራ ቢያልቅና ብንዘግበው ያንንም አጀንዳ ውሸት ነው ብሎ እንደሚያስጥለን የሚያሳይ ነው፡፡ አሳፋሪ አክቲቪዝም!
የአብይ ቡድን ስራውን እየሰራ ነው፡፡ መጪው ጭፍጨፋ ከእናርጅ እናውጋ እየበለጠ እንደሚሄድ መጠራጠር አይገባም፡፡ የጅምላ እስሩና ስቃዩ፣ ስደቱ፣ አንገት መድፋቱ ሁሉ እየመጣ ነው፡፡ ይህን እጅግ አስቀያሚ ሁኔታ መቀልበስ ግን ይቻላል፡፡ የችግሩም ሆነ የመፍትሄው ምንጮች ደግሞ እኛው ነን፡፡ ሌላ ቦታ ማንጋጠጥ አይገባም፡፡
መፍትሄው በየእለቱ የሚጠቃው ህዝባችን ጥቃትና ውርደት ተሰምቶን ለህዝባችን ስንል፣ ከእርስ በእስር መጠፋፋት፣ ከእርስ በእስር ጥላቻ፣ ከቂምና ከበቀል መራቅ እና “ያለፈው አለፈ” ብሎ መተባበር ብቻ ነው፡፡ መፍትሄው “እኔ ብቻ ነኝ ትክክል፣ የእኔ መንገድ ብቻ ነው ትክክሉ” ከሚል ከንቱና ፍሬ ቢስ አስተሳሰብ እርቆ ለህዝብ ህልውናና ጥቅም ሲባል መተባበር ነው፡፡ መፍትሄው ለጋራ አሸናፊነት ሲባል መሸነፍ ነው፡፡ መፍትሄው ራስን ከከፋፋይ አክቲቪስት ማራቅ ነው፡፡ መፍትሄው ራስን፣ ትግሉንና የጠላትን ሁኔታ በየጊዜው መገምገምና ሁኔታው የሚጠይቀውን ስትራቴጂ መቅረጽ ነው፡፡ መፍትሄው በእቅድ መመራት ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ዋናውና ቁልፉ መፍትሄ በአማራ ብሄርተኝነት ርእዮት መመራት ነው፡፡
ከንቱዎች እንደሚሉትና እንደሚመስላቸው ከትግሉ ሜዳ እስክንድር ነጋ ባይኖር ወይም ሌሎች ከንቱዎች እንደሚመስላቸው ዘመነ ካሴ ቢወጣ የሚመጣ አንዳችም ለውጥ የለም፡፡ የአማራ ትግል ችግር ከእነዚህ ግለሰቦች በላይ በመሆኑ የእነዚህ ግለሰቦች መኖር አለመኖር ጋር ሊያያዝ አይችልም፡፡ ስለሆነም ከግለሰቦች ራስ ወርዶ (ከማሞገስና ከማኮሰስ ተቆጥቦ) በድርጅት ግንባታ ላይ ማተኮር ነው፡፡ እንደ ህዝብ የእኛ ትልቁና ቋሚው ድክመታችን የድርጅት ግንባታ ችግር ነው፡፡ ይህን ፈተና ሳናልፍ የምናመጣው አንዳችም ለውጥ የለም፡፡ ስለሆነም ከዋናው ጠላት በላይ ግለሰቦችን ዋነኛ ኢላማ በማድረግ ጎራ ለይቶ መጠፋፋቱ የጋራ ውድቀትን ካልሆነ በስተቀር የሚያስገኘው አንዳችም ውጤት የለምና ከዚህ የጥፋት ጎዳና መውጣት ይጠበቅብናል፡፡ ኋላቀርነት ይብቃ! ከጠላት ይልቅ በጠላት ላይ መጨከን ይብቃ!
ይህ ሳይሆን ቀርቶ የፋኖ ትግል አሁን ባለበት የእውር-ድንበር ጎዳና የሚቀጥል ከሆነ ግን እንኳን ህዝብን ነፃ ሊያወጣ የራሱንም ህልውና መጠበቅ አይችልም፡፡ ከመንቦጅቦጅ ወጥቶ የሰከነ የትግል ምህዋር ውስጥ መግባት ግዴታ ነው፡፡
የወገኖቻችንን መስዋእትነት ወደ ሞት እንዳንቀይረው እንጠንቀቅ!
ለገባንበት መቀመቅ ዋነኛዎቹ ተጠያቂዎች እኛው ራሳችን መሆናችንን እንቀበል!
አማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!!!