ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


The best fiction is far more true than any journalism
📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ
👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56
👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


👆👆👆👆

የ50 ሚሊዮን ብር ሎተሪ ለማሸነፍ በ200 ብር አሁኑኑ ይቁሩጡ!

#ዳጉ_ጆርናል




ዳጉ ጆርናል-ስፖርት dan repost
የፓሪስ ሴንት ዠርሜይን ደጋፊዎች በቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ "በጋዛ ውስጥ ያለውን የዘር ማጥፋት ይቁም" የሚል ባነር አሳዩ

የፓሪሱ ቡዱን ደጋፊዎች አሽራፍ ሃኪሚ በ12ኛው ደቂቃ ላይ ጎል አስቆጥሮ ኢንተር ሚላንን 1-0 መምራት ከጀመሩ በኋላ ነው ባነሩን ያሳዩት። ዲዜሪ ዱዌ የPSG ሁለተኛ ጎል ሲያስቆጥርም  ባነሩ በአልያንዝ አሬና ውስጥ ይታይ ነበር።

የፒኤስጂ ደጋፊዎች የጋዛ ጦርነት እንዲቆም ባላቸው አቋም የሚታወቁ ሲሆን ከዚህ ቀደም በህዳር ወር ላይ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር በተደረገው የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ላይም “ነፃ ፍልስጤም” የሚል ግዙፍ ባነር ማሳየታቸው አይዘነጋም።

በሚሊዮን ሙሴ

በሌሎች የስፖርት ቻናሎች ላይ የማያገኟቸዉን የስፖርታዊ መረጃዎችን በይፋዊ የዳጉ ጆርናል ስፖርት ቻናል https://t.me/Dagujournalsport ላይ ያገኛሉ።

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት


ዳጉ ጆርናል-ስፖርት dan repost
የ19 ዓመቱ ኮኮብ ዴዜሪ ዱዌ በቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ከአንድ በላይ ጎል ያስቆጠሩ ተጨዋቾች ዝርዝር ተቃለቀለ

👉 በቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ከአንድ በላይ ጎል ያስቆጠሩ 8 ተጨዋቾች ብቻ ናቸው።



በቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ከአንድ በላይ ጎል ማስቆጠር የቻሉ ተጨዋቾች እነማን ናቸው የሚለውን ስንመለከት ደግሞ:-

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ

⚽️ ጋርዝ ቤል በ2018 ማድሪድ ሊቨርፑልን 3ለ1 ሲያሸንፍ 2 ጎል

⚽️ ሄርናን ክሪስፖ በ2005 ኤስ ሚላን ከሊቨርፑል 3ለ3 ባለቀው ጨዋታ (ሊቨርፑል በመለያ ምት ያሸነፈበት) 2 ጎል

⚽️ ፊሊፖ ኢንዛጊ በ2007 ኤስ ሚላን ሊቨርፑልን 2ለ1 ባሸነፈበት ጨዋታ 2 ጎል

⚽️ ዳኒኤሌ ማሳሮ በ1994 ኤስ ሚላን ባርሴሎናን 4ለ0 ባሸነፈበት ጨዋታ 2 ጎል

⚽️ ዲያጎ ሚሊቶ በ2010 ኢንተር ባየርን 2ለ0 ባሸነፈበት ጨዋታ 2 ጎል

⚽️ ካርል ሄንዝ ሪድል በ1997 ዶርትመንድ ጁቬንቱስን 3ለ1 ባሸነፈበት ጨዋታ

⚽️ ክርስትያኖ ሮናልዶ ማድሪድ ጁቬንቱስን 4ለ1 ባሸነፈበት ጨዋታ 2 ጎል

⚽️ ዴዝሪ ዱዌ በ2025 ፒኤስጂ ኢንተርን 5ለ0 ባሸነፈበት ጨዋታ 2 ጎል (NEW)

ፑስካስ በ1960ው የዩሮፕያን ካፕ ማድሪድ ፍራንክፈርትን በገጠመበት ጨዋታ 4 ጎል ማስቆጠሩ አይዘነጋም። ዲስቲፋኖም በተመሳሳይ በጨዋታው 3 ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን ጨዋታውም 7ለ3 በሆነ ውጤት ነበር የተጠናቀቀው።

በሚሊዮን ሙሴ

ለስፖርታዊ መረጃዎች ይፋዊ የዳጉ ጆርናል ስፖርት ቻናል https://t.me/Dagujournalsport ን ይቀላቀሉ።

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት


ከስድስት ዓመታት በፊት በካንሰር ያጣት ልጁ ዣናን የሚያስታውስ አጋጣሚ ❤️👼🏼 🥺

የዘጠኝ ዓመት ዕድሜ የነበራት ይህች ልጁ ከባርሤሎና ጋር የሻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ ሲያነሳ ያኔ ከጎኑ በሜዳ ውስጥ ስትቦርቅ ነበር 🥺 ከብዙ መከራና ስቃይ በኋላ ዛሬ ፊቱ ላይ ፈገግታ ታይቷል ❤️✨

Luis said: “My daughter came on the earth to live with us for 9 wonderful years and 𝐬𝐡𝐞’𝐬 𝐚𝐥𝐢𝐯𝐞… because we remember her. Xana’s not here in the physical sense… but she will be here with us spiritually, always”. ❤️‍🩹

@mikoethio
#ዳጉ_ጆርናል


የ2025ቱ ሻምፒዮንስ ሊግ ሻምፒዮኑ ፒኤስጂ


12ዓመታትን በክለቡ የቆየው ብራዚላዊዉ ተከላካይ እናም የቡድኑ አምበል ማርኪኒሆስ ይህን ስኬት ለዓመታት ጠብቋል

#ዳጉ_ጆርናል


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ለክለቡ ሁሉን የሚሰጠው ባለሀብት 👌

#ዳጉ_ጆርናል


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ዋንጫውን ከፍ አድርገዋል

#ዳጉ_ጆርናል


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
Paris 🔥


የአራትዮሽ ዋንጫ አሸናፊው ፓሪስ ሴንት ጀርሜን

👉 ሊግ ኧ
👉ሻምፒዮንስ ሊግ
👉 ኩፕ ደ ፍራንስ
👉 ትሮፊ ዴስ ሻምፒዮንስ

@mikoethio
#ዳጉ_ጆርናል


ፒኤስጂ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ

👉 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ አሸናፊ ሁነዋል



ፓሪሰንዠርመ 5-0 ኢንተር ሚላን

ሀኪሚ 13'
ዱየ 20' 64'
ክቫራትስኬሊያ 72'
ሙዩሉ 87'

👉 በሻምፒዮንስ ሊግ ታሪክ በፍፃሜው ጨዋታ በዚህ መልኩ ግብ ሲቆጠር መመልከት አልተለመደም 😂 የ ሉዊስ ኤነሪኬ አስደናቂ ስራ ውጤት ነው ።

#ዳጉ_ጆርናል


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ፒኤስጂ

👉 የ2024/25 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ አሸናፊ

                      
   ፓሪሰንዠርመ 5-0 ኢንተር ሚላን
    
ሀኪሚ 13'
ዱየ 20' 64'
ክቫራትስኬሊያ 72'
ሙዩሉ 87'

#ዳጉ_ጆርናል


ፒኤስጂ 4-0 ኢንተር


ጤና ሚኒስቴር፦ በኢትዮጵያ የMpox (የዝንጀሮ ፈንጣጣ) የመጀመሪያ ሞት ተመዘገበ።

#ዳጉ_ጆርናል


በሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ፒኤስጂ በአሽራፍ ሃኪሚ እና ዲሳየር ድዌ ግብ ኢንተርሚላንን 2 ለ 0 በመምራት ላይ 🔥

#ዳጉ_ጆርናል


👆👆👆👆

የ50 ሚሊዮን ብር ሎተሪ ለማሸነፍ በ200 ብር አሁኑኑ ይቁሩጡ!

#ዳጉ_ጆርናል




በህንድ በተከናወነው የ ሚስ ወርልድ የቁንጅና ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ሀሴት ደረጄ 2ኛ ወጣች

ኢትዮጵያዊቷ ቆንጆ ከአለም 2ተኛ ከአፍሪካ 1ኛ በመሆን ውድድሩን ያጠናቀቀች ሲሆን በዚህ ውድድር ከ109 አገራት ቆነጃጅት ጋር ለ አንድ ወር ያህል የፈጀ ውድድር ስታደርግ ቆይታለች::

በውድድሩ የኢትዮጵያን እሴቶች በማስተዋወቅ እና የሀገሯን ገፅታ በተገቢው መልኩ በማሳየት ላደረገችው ጥረት የቱሪዝም ሚኒስቴር ያለውን ምስጋና ገልጿል።

#ዳጉ_ጆርናል


ማይቻርጅ ቴክኖሎጂ በሞባይል መተግበሪያ የታገዘ የፓወር ባንክ ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ

ማይቻርጅ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ የመጀመርያ የሆነውን የጋራ የፓወር ባንክ ኪራይ ቴክኖሎጂ ወደ ሃገር ውስጥ በማሰገባት ስራ ከጀመረ ወራትን አሰቆጥሯል።

ማይቻርጅ ቴክኖሎጂ በዘመናዊ ሞባይል መተግበሪያ እና ዘመኑ በደረሰባቸው ፓወር ባንክ ማከራያ ጣቢያዎች በመታገዝ በአንድ scan
በቅርብ ቦታ ካለ ጣቢያ፣ ፓወር ባንክ በመውሰድ ቻርጅ የሚያረጉበት ቴክኖሎጂ ነው ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ አብደላ ደጋሎ ተናግረዋል።

የማይቻርጅ ቴክኖሎጂ ሰርቪሶቹን ለመጠቀም የሚያስፈልገው ሞባይል መተግበሪያ ማውረድ እና መተግበሪያውን ተጠቅመው በአቅራቢያ የሚገኝ ጣቢያ ጋር በመሄድ QR code scan ማድረግ ብቻ ነው ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለው ገልፀዋል።

ድርጅታችን አገልግሎቱን ከጀመረ ገና 4 ወር የሆነው ቢሆንም በአሁኑ ሰዓትም ከ 5000
በላይ የማይቻርጅ መተግበሪያ ተጠቃሚ አፍርተናል ሲሉ የማይቻርጅ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ናሆም ሰለሞን ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም በአዲስ አበባ ውስጥ ከ60 ቦታዎች በላይ የማከራያ ጣቢያዎቻችን ማግኘት ይቻላል ብለዋል።

በቦሌ፣ ፒያሳ፣ ሜክሲኮ፣ 4ኪሎ፣ ካሳንቺስ፣ መስቀል ፍላወር፣ ሰሚት፣ ቤቴል፣ ጀሞ እና ለቡ ባሉ ሰፈሮች ላይ እንደ ቶሞካ ቡና፤ ኦልማርት ሱፐር ማርኬት፣ ሞሞና ሆቴል፣ አኮ ቡና፣ ሶራምባ ሆቴል፣ ዉዳሴ ዲያግኖስቲክ ሴንተር፣ ዴቦኒየርስ ፒዛ፣ ሌቤንዝ ህንፃ፣ ዮናስ ጨርጨር እና ፍቅሬ ኩንስፓኛ በመሰሉ አጋር ድርጅቶች ውስጥ እንገኛለን ሲሉ አቶ ናሆም ሰለሞን ገልፀዋል፡፡

ማይቻርጅ በቀጣይም እስከ አመቱ መጨረሻ ከ150 በላይ ቦታዎች ላይ በመላው አዲስ አበባ
የመገኘት እቅድ የያዘ ሲሆን ከመላው ሃገሪቱ አልፎም በጎረቤት ሃገራት ድንበር ለመሻገር እቅድ መያዙን ብስራት ሰምቷል። ማይቻርጅ በቅርቡም በማይቻርጅ መተግበሪያ የታገዘ ዘመናዊ እና ቀላል የኤሌትሪክ መኪና እና ሞተር ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

በሰላማዊ ነጋሲ
#ዳጉ_ጆርናል

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.
OSZAR »