“ ያለፍርሃት ወደ ሜዳ እንገባለን “ ሲሞን ኢንዛጊ
የኢንተር ሚላኑ ዋና አሰልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊ ከነገ ምሽቱ የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በፊት ለጋዜጠኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊ ምን አሉ ?
- " ፓቫርድ በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ጥሩ ልምምድ ነበረው ጥሩ ቁመና ላይ ከሆነ በቋሚነት ይጀምራል እሱ አስፈላጊ ተጨዋቻችን ነው።
- በኢንተር ሚላን ጥሩ ስሜት ይሰማኛል ስኬታማ ለመሆን አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ አሉኝ አሁን የሁላችንም ሀሳብ ፍፃሜው ነው።
- ከፍፃሜ ጨዋታው በኋላ ከክለቡ አስተዳደር ጋር ለንግግር እቀመጣለሁ ለኢንተር ሚላን ጥሩውን ነገር እንወስናለን።
- በፍፃሜው የተሸናፊነት ግምት ይሰጠናል ከሁለት አመት በፊትም ይህ አስተሳሰብ ነበር ነገርግን ከማንችስተር ሲቲ እኩል ነበርን እስከመጨረሻውም ተፎካክረናል።
- በእግርኳስ በገንዘብ ወይም በደሞዝ አይደለም ጨዋታው የተጨዋቾቹ ፍልሚያ ነው እነሱ ናቸው ሁሉንም የሚወስኑት።
- ያለምንም ፍርሀት ወደ ሜዳ መግባት አለብን ጨዋታውን ማሸነፍ እንዳለብን ልናውቅ ይገባል የመጣንበት መንገድ በራስ መተማመናችንን ጨምሮታል።"ብለዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe