ፍርድ ቤቱ አቶ ታዬ ዳንዳአ ነፃ የተባሉበት ሁለቱ ክሶች በድጋሚ ክርክር አንዲደረግባቸው አዘዘ‼️
ከአንድ አመት በፊት ከሰላም ሚኒስተር ዴኤታነት የተነሱት እና በቁጥጥር ስር ውለው በሶስት ክሶች ተከሰው፤ በሁለቱ ክሶች ነፃ የተባሉት አቶ ታዬ ዳንዳአ ክሶቹ በድጋሜ እንዲቀጥሉ ውሳኔ ተላለፈባቸው።
በአቶ ታዬ ላይ ነፃ የተባሉበት ሁለቱ ክሶች "ከጠላት ጋር በመተባበር" እና "የፀረ-ሰላም ቡድኖች የሆኑትን ሸኔ እና ፋኖን የሚደግፉ መልዕክቶችን" በፌስቡክ ገፃቸው አጋርተዋል ከሚሉት ክሶች ነው።
የቀደሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታው ከቀረቡባቸው ሦስት ክሶች መካከል ሐምሌ 30 በዋለው ችሎት በ1ኛ እና በ2ኛ ክስ ነጻ የተባሉ ሲሆን የጦር መሳሪያ ወንጀሎችን በተመለከተ የቀረበባቸውን ሶስተኛው ክስ ተለቀው እንዲከላከሉ ብይን መሰጠቱም ይታወሳል፡፡
አቶ ታዬ ህዳር 23 ቀን 2016 በዋለው ችሎት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዋስትና እንዲፈቱ መወሰኑን ተከትሎ ህዳር 26፣ 2016 ዓ/ም ከእስር ቤት ወጥተው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ ነበር።
ይሁን እንጂ አቃቤ ህግ አቶ ታዬ ከተመሰረተባቸው ሁለቱ ክሶች ነፃ መባል የለባቸውም በሚል ይግባኝ በማለቱ ጉዳዩ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቷል።
በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ዛሬ ቀጠሮ የሰጠው ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግን ይግባኝ በማጽናት አቶ ታዬ ነፃ በሆኑበት ሁለቱ ክሶች እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል።
በመሆኑም ክሶቹ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደሚመለሱና ክርከሩ እንደሚቀጥል ጠበቃቸው መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ከሶስቱ ክሶች መካከል በሁለቱ ነጻ በመባላቸው የከበረላቸው የዋስትና መብታቸው ይነሳል ወይስ አይነሳም የሚለው በቀጣይ ቀጠሮ የሚታወቅ ይሆናል ብለዋል።
@ethio_mereja_news@ethio_mereja_news