ኢትዮ መረጃ - NEWS


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@B_promotor

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


‹‹ሂውማን ራይትስ ፈርስት ኢትዮጵያ›› በመንግስት ላይ ሰብአዊ መብት የመጣስ ክስ ሊመሰርት ነው‼️

አገር በቀል የሆነው ሂውማን ራይትስ ፈርስት ኢትዮጵያ የተሰኘው የመብት ተሟጋች ተቋም መንግስት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተፈናቃዮችን ወደቤታቸው ባለመመለሱ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፅሟል በሚል ክስ ለመመስረት መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡

የተቋሙ ዳይሬክተር አቶ ተስፋለም በርሄ በዚህ ጉዳይ ላይ ዝግጅታቸውን እያጠናቀቁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ሲናገሩም ‹‹ተፈናቃዮች ወደቤታቸው እንዲመለሱ በፍርድ ቤት ውሳኔ ማስገደድ ይቻል እንደሆነ ወደፊት የምናየው ይሆናል፡፡ ነገር ግን እኛ ጉዳዩን ወደህግ መውደስ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል›› ብለዋል፡፡

ተፈናቃዮች ወደቤታቸው ባለመመለሳቸው የሰብአዊ ቀውሱ መባባሱንና የከፋ ሁኔታ ላይ ማድረሱን ጠቀሱት ዳይሬክተሩ ጨምረውም ‹‹ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉት ሰዎች ለሶስትና ለአራት አመታት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከመኖራቸውም በላይ አሁንም እየተሰቃዩ ናቸው›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

እንደአቶ ተስፋለም ገለፃ፣ ተፈናቃዮችን በፈቃደኝነት ወደቤታቸው መመለስ የሰብአዊነት ስራ ብቻም ሳይሆን በአገርና በአለም አቀፍ ህግ የተቀመጠ ግዴታም ነው፡፡ የአፍሪካ ህብረት የካምፓላ ስምምነትና የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ይህንን በግልፅ ማስፈራቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ መንግስት ተፈናቃዮችን የመመለስ አስቸኳይ እርምጃ የማይወስድ ከሆነ ድርጅታቸው በእነዚህ ህጋዊ መሰረቶች ወደክስ ለማምራት እንደሚገደድም አሳስበዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


ተፈቀደላቸው‼️

ወደ ትግራይ እቃ ጭነው እንዳይገቡ ተከልክለው የነበሩ መኪኖች ተፈቀደላቸው

ወደ ትግራይ ክልል ሲጓዙ አፋር ላይ ለቀናት ክልከላ የተደረገባቸው ተሽከርካሪዎች እንዲለቀቁ መወሰኑ ተገልጿል።

ውሳኔውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ጋር መወያየታቸው ተከትሎ ነው ተግባራዊ የሆነው።

ፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ግንቦት 23/ 2017 ዓ/ም ከኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ጽህፈት ቤታቸው ባወጣው መግለጫ ላይ ጠቅሷል።

በዚህም ከግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ  በአፋር በኩል ወደ ትግራይ ሲጓዙ ክልከላ የተደረገባቸው የጭነት ተሽከርካሪዎች የተከለከሉበት ምክንያት የጫኑት የንግድ እቃ ከትግራይ አልፎ በኮንትሮባንድ መልክ ወደ #ኤርትራ ሊሻገር ይችላል ከሚል ጥርጣሬ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተገልጿል።

ሁለቱም ኃላፊዎች በውይይታቸው የመረጃው  እውነትነቱ ምን ድረስ እንደሆነ የሚያጣራ ከፌደራል ፖሊስ እና ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተውጣጣ ኮሚቴ ጉዳዩን እንዲመረምረው ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ይህ ደግሞ ትናንት ቅዳሜ ምሽት በፔፕሲ የሚሊኒየም ዝግጅት ላይ የታዬ ክስተት ነው።የፌደራል ፖሊስ አባል ከአንድ ወጣት ጋር ሲጋጭ ይታያል።ኃይል መፈታተሽ


@Ankuar_mereja
@Ankuar_mereja


ለምን የጠየኩትን አላገኘሁም?  

ሰው መሆን በራሱ ወደ ላይ ማንጋጠጥ፣ አንዱ ጥያቄ ሲመለስ ሌላ መጠየቅ፣ አንዱ ፍላጎት ሲሟላ ሌላኛው ላይ ማተኮር ያለበት ነው፡፡ አንዳንዴ ሌሎች በቀላሉ የሚያገኟቸው እኛ ግን ነጋ ጠባ ፈጣሪያችንን ወትውተን ያላገኘናቸው ነገሮች ይኖራሉ፡፡ አልፎ ተርፎም ይህ አጥብቀን የምንሻው ነገር ሊኖረን እንደሚገባ በበርካቶች ዘንድ የሚታመንበት፣ ጥቂት የማይባሉ ሰዎችም እርግጠኛ ሆነው እንዳለን የሚያስቡት እኛ ግን ያላስተዋልነው ይሆናል፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥም ቢሆን እንኳ፣ እንደ ክርስቲያን እያመሰገንን በተስፋ መጠበቅ በራሱ ትልቅ ዋጋ ያሰጣል፡፡ አንዳንዴ ግን ጥያቄያችን መልስ ሲያጣ ለምን ብለን እንጠይቅ፡፡ በረከቱ ይደርብንና ታላቁ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “እግዚአብሔርን ደጋግመህ ጠይቀኸው ያልሰጠህ ነገር ካለ፣ አንተን ደጋግመው ጠይቀውህ ያልሰጠሃቸው ሰዎች እንዳሉ አስብ፡፡” ይለናል፡፡ 

የበርካታ ቅዱሳንና ጻድቃን ወላጆች ልጅ አጥተው ለበርካታ ዓመታት ፍሬ እንዲሰጣቸው ሲማጸኑ ኖረው ሁሉም ነገር አበቃለት ሲሉ እግዚአብሔር ምላሽ ሰጥቷቸዋል፡፡ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወላጆች ቅዱሳኑ ኢያቄም ወሐና፣ ይስሐቅን ያገኙት አባታችን ቅዱስ አብርሃምና ቅድስት ሳራ፣ መጥምቀ መለኮትን የወለዱት ካሕኑ ቅዱስ ዘካርያስና ቅድስት ኤልሳቤጥ ለዚህ ምሳሌ ናቸው፡፡ በሕገ እግዚአብሔር ጸንተው እየኖሩ ልመናቸውን ሳይታክቱ በመቀጠላቸው እመአምላክንና ቅዱሳንን መውለድ ችለዋል፡፡ በበርካታ መከራ ውስጥ አልፈው ምድራዊ ኃይል አለኝ ባለ ንጉስ ተለያተው ዳግም የተገናኙት ቅዱሳን ጸጋ ዘአብና እግዚእ ሃረያ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ወልደዋል፡፡ እግዚአብሔር “ፈታሒ በጽድቅ ኮናኒ በርትዕ“ ነውና እንደ የስራችን ይከፍለናል፡፡ ለልባዊ ጸሎታችን ዋጋ ይሰጠናል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለው አንዳንዴ ግን ሲጠሩን ያልሰማናቸው ይኖሩና ጥቄያችን መልስ ላይገኝ ይችላል፡፡ እገዛችንን ልንሰጣቸው እየቻልን አልፈናቸው የሔድን ስንቶች ናቸው? ጩኸታቸውን እንዳንሰማ መስኮታችንን የዘጋንባቸው፣ ወይም ዳንኪራችንን ከፍ አድርገን ጩኸታቸውን የዋጥንባቸው ስንቶች ናቸው? የትኛውን ጥሪ ነው በአጽንኦት የሰማነው? ስለበደላችን በቀራንዮ አደባባይ “ኤሎሔ… ኤሎሔ… ላማ ሰበቅታኒ” አባት ሆይ ለምን ተውኸኝ ያለው ጥሪ የኛ አይደለምን? እርሱ የሁሉ ባለቤት ሲሆን “ተጠማሁ” ማለቱ የኛን መጠማት ለማርካት ደሙን ሲያፈስ ያሰማው ነው፡፡ ሞቱ፣ ግርፋቱ… የኛን ሞትና ግርፋት የተቀበለበት ፍጹም ፍቅሩ የተገለጸበት ድንቅ ስጦታው ነው፡፡ ይህን ያህል ዋጋ የከፈለልን አምላክ፣ ለጥቂቷ ዓለማዊ ጥያቄያችን ደጋግመን ጠይቀን ካልተሰጠን ወደ ራሳችን እንመልከት፡፡

ቅዱሳኑ በብጽአት ያገኟቸውን ቅዱሳን ፍሬዎች እነ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና ኢትዮጵያዊው ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ሌሎችንም አርአያ ያደረጉ በአስቸጋሪ ሁኔታ የበረሀው ሐሩር የሌት ቁር የሚፈራረቅባቸው፣ ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው፣ ግርማ ሌሊቱን፣ ድምጸ አራዊቱን፣ ጸብአ አጋንንቱን ታግሰው፣ ዓለምን ንቀው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ በሚገኘውና ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አድነት ገዳም በርካታ ገዳማውያን መነኮሳት ይኖራሉ፡፡ መነኮሳቱና ገዳማውያኑ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች እየተፈታተኗቸው ነውና በዓታቸውን ለማጽናት እጃችንን እንድንዘርጋ፣ ሌሊትና ቀን በትጋት የሚቆሙበት ጸሎታቸው፣ ምድራዊ ያልሆነ ረድኤታቸው ተካፋይ እንሁን፡፡ የአግዙን ጥሪያቸውን እንስማቸው!!!   


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




በመዲናችን አዲስ አበባ ሰው አልባ ፖሊስ ጣቢያ ሊኖር መሆኑ ተሰምቷል‼️

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
ኮሚሽነር ጄነራል ደምመላሽ ገብረሚካኤል እንደገለፁት አዲስ አበባ ከወራት በኋላ በአፍሪካ የመጀመሪያው፣ በአለም ደግሞ አራተኛው ሰው አልባ ስማርት ፖሊስ ጣቢያ ባለቤት ትሆናለች ብለዋል።
ይህ ጣቢያ ሲጀመር፣ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ያለምንም ንክኪ ጉዳዩን ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ የሚችልበት እና የሚፈልገውን የፖሊስ ሀላፊ በቀጥታ አግኝቶ ችግሩን ማስረዳት የሚያስችል ስርዓት ይዘረጋል።

እንዲሁም አሁን ላይ ህብረተሠቡ በአዲስ አበባ በምሽት በነጻነት ስፖርት መስራት ይቻላልም ሲሉ ገልፀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

6.8k 0 10 11 65

ሰበር‼️

ኢትዮጵያዊቷ ቆንጆ ከአለም 2ተኛ ከአፍሪካ 1ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀቀች፡፡

በህንድ እየተከናወነ ያለው ሚስ ወርልድ የቁንጅና ውድድር አሁን ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ በዚህ ውድድር የ109 አገራት ቆነጃጅት የተሳተፉ ሲሆን ‹‹ሚስ ወርልድ›› የሚል መጠሪያ በማግኘት የዘንድሮውን ዘውድ የጫነችው ታይላንዳዊቷ ኦፓል ሱቻታ ሆናለች፡፡

እሷን ተከትላ ኢትዮጵያን የወከለችውና በውድድሩ ላይ ‹‹ሚስ ኢትዮጵያ›› ተብላ ስትጠራ የነበረችው ሀሴት ደረጄ 2ተኛ ሆናለች፡፡ ሀሴት ከአለም 2ተኛ ትሁን እንጂ ከአፍሪካ 1ኛ በመሆን ከአህጉሪቱ ቆነጃጅት ሁሉ ቀዳሚ በመሆን አሸናፊ መሆኗን የውድድሩ አዘጋጆች አስታውቀዋል፡፡

ከአለም 3ተኛ የወጣችው የፖላንድ ተወዳዳሪዋ ስትሆን የማርቲንኪ ተወዳዳሪዋ 4ተኛ ሆናለች፡፡ ይህ ውድድር ለአንድ ወር በህንድ የተለያዩ ግዛቶች ሲከናወን ቆይቷል፡፡

#MissWorld2025 #MissEthiopia

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


ጦር መሣሪያ ግዢ ማዕቀቡ ተራዘመ‼

የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በደቡብ ሱዳን ላይ የተጣለውን የጦር መሣሪያ ግዢ ማዕቀብ ለተጨማሪ አንድ ዓመት አራዘመ።

የርስ በርስ ጦርነት አፋፍ ላይ ቆማለች የሚል ሥጋት ባረበበባት ደቡብ ሱዳን ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲራዘም ምክረ-ሐሳብ የቀረበው በአሜሪካ አማካኝነት ሲሆን የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያጸደቀው በጠባብ የድምጽ ልዩነት ነው።

ከ15 የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት መካከል ትላንት ዓርብ በነበረው ድምጽ አሰጣጥ ዘጠኙ የውሳኔ ሐሳቡን ደግፈዋል።

የውሳኔ ሐሳቡ ያገኘው የድጋፍ ድምጽ ለመጽደቅ ከሚያስፈልገው ዝቅተኛው ነው።

ስድስት ሀገራት ማለትም ሩሲያ፣ ቻይና፣ አልጄሪያ፣ ሴራ ሊዮን፣ ሶማሊያ እና ፓኪስታን ድምጸ ተዓቅቦ አድርገዋል።

በክራይስስ ግሩፕ የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ተንታኝ የሆኑት ዳንኤል አኬች የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ የጦር መሣሪያ ግዢ ማዕቀቡን ማራዘሙ በደቡብ ሱዳን ሊከሰት የሚችለውን ግጭት መጠን ለመቀነስ የሚያግዝ ጠቃሚ እርምጃ እንደሆነ ገልጸዋ

via DW

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


83 በመቶ የሚሆነው የትራፊክ አደጋ የሚከሰተው በአሽከርካሪዎችና በተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ችግር ምክንያት መሆኑ ተገለጸ!

በከፍተኛ ደረጃ እየተከሰተ ካለው የትራፊክ አደጋ ውስጥ 69 በመቶ ገደማ የሚሆነው በአሽከርካሪዎች እና 14 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ምክንያት የሚከሰት መሆኑን የመንገድ ደህንነት እና መድህን ፈንድ አገልግሎት ለአሐዱ ገልጿል።

በሀገሪቱ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ የመጣው የትራፊክ አደጋ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጹት በአገልግሎቱ የመንገድ ደህንነት ትምህርትና ግንባታ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዮሐንስ ለማ፤ ለአደጋው መጨመር ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም በዋናነት የአሽከርካሪዎች ቸልተኝነት ተጠቃሽ መሆኑን ተናግረዋል።መሪ ሥራ አስፈፃሚው አክለውም የእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም ችግር፣ የመንገድ ሁኔታ እና በተለይ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከልክ በላይ ፍጥነት ማሽከርከር ለአደጋው ተጋላጭ የሚያደረጉ መንስኤዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

"አደጋው የሰው ሕይወት ከማጥፋቱ በተለይም አምራች የሚባለውን የሀገሪቱን ወጣት እያሳጣን ነው" ያሉት አቶ ዮሐንስ፤ በንብረት ውድመት ላይ እየደረሰ ያለው ምጣኔ ሃብታዊ ኪሳራ ቀላል የሚባል አለመሆኑን አንስተዋል።የትራፊክ አደጋው በአብዛኛው ከ5 እስከ 30 የእድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ የሚከሰት ሲሆን፤ አደጋውን የሚያደርሱት ደግሞ ከ18 እስከ 30 እድሜ ያሉ አሽከርካሪዎች እንደሆኑም አቶ ዮሐንስ ጠቁመዋል።

በ2016 ዓ.ም በንብረት ላይ በደረሰ አደጋ ብቻ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን አስታውሰዋል።የትራፊክ አደጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ አደጋው በትራፊክ ፓሊስና የሚመለከተው ባለድረሻ አካል ቁጥጥር ብቻ መቀነስ ስለማይቻል ሁሉም በጋራ ሊሰራ እንደሚገባ መሪ ሥራ አስፈፃሚው አሳስበዋል።


ሀገሩ ፍልስጤም ልዩ ስሟ “ልዳ” ሲሆን የተወለደው በ277 ዓ.ም ጥር 20 ቀን ነው፡፡

አባቱ የልዳ መኳንንት ዞሮንቶስ ወይም አንስጣስዮስ፣ እናቱ ቴዎብስታ ወይም አቅሌስያ ከእርሱ ሌላ ማርታና እስያ የሚባሉ ሁለት ሴት ልጆች ነበሯቸው፤ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ፡፡ የስሙ ትርጓሜ “ኮከብ ብሩህ፣ ፀሐይ” ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዐሥር ዓመት በሆመው ጊዜ አባቱ ስለሞተ ሌላ ደግ ክርስቲያናዊ መስፍን ወስዶ በጦር ኃይል አሰለጠኖ አሳደገው፡፡ በሃያ ዓመቱም መስፍኑ የ15 ዓመት ሴት ልጁን ሊያገባው ሲያስደግስ ጌታችን ለዚህ አላጨውምና የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ኀዘኑን ጨርሶ ወደ ቤሩት ከተማ ሄደ፡፡ በዚያም የሚመለክና ሴት ልጆቻቸውን የሚገብሩለትን ደራጎን ገድሎ ሕዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር አስገብቷቸዋል፡፡ ወደፋርስም ሲሔድ ንጉሱ ዱድያኖስ ሰባ ነገሥታት ሰብስቦ ሰባ ጣዖታት ሲያመልኩ ቢያገኛቸው በነገሥታት ፊት የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፡፡


ዱድያኖስም ማንነቱን ከተረዳ በኋላ “አንተማ የኛ ነህ በዐሥር አህጉር ላይ እሾምሃለሁ የኔን አምላክ አጵሎንን አምልክ” አለው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም “አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ላን ሹመት አልክደውም” አለው፡፡ ዱድያኖስም እጅግ ተናዶ ብዙ አሠቃቂ መከራዎችን አደረሰበት፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ጌታችንን “ይህን ከሃዲ እስካሳፍረው ድረስ ነፍሴን አትውሰዳት” በማለት ለመነው፡፡ እግዚአብሔርም ጽናትን ሰጥቶታል፡፡ የደረሱበት እጅግ አሠቃቂ መከራዎች የሰው ኅሊና ሊያስባቸው እንኳን የማይችላቸው ናቸው፡፡ በእንጨት ላይ ሰቅለው ሥጋውን በመቃን አስፈተተው፣ ረጃጅም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማ አጫምተው ሂድ አሉት፡፡ ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልን ልኮለት ፈውሶታል፡፡ ዳግመኛም በሰባ ችንካሮች አስቸንክሮ በእሳት አስተኩሶ አናቱን በመዶሻ አስቀጥቅጦ በሆዱ ላይ የደንጊያ ምሰሶ አሳስሮ እንዲያንከባልሉት አደረገ፡፡

በመጋዝ ሰውነቱን አስተልትሎ ጨው ሲነሰንስበት ሥጋው መሬት ላይ ወደቀ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት በእጁ ዳስሶ ፈወሰውና “ገና ስድስት ዓመት ለስሜ ትጋደላለህ፣ 3 ጊዜ ትሞታለህ፣ በ4ኛውም ታርፋለህ፣ በመከራህም ሁሉ አልለይህም አለው፡፡ ዱድያኖስም ቅዱስ ጊዮርጊስን “ለሚያሸንፍልኝ ብዙ ወርቅ እሰጠዋለሁ” አለ፡፡ አንድ መሰርይ መርዝ ቀምሞ አስማተ ሰይጣን ደግሞበት ለቅዱስ ጊዮርጊስ አጠጣው። ሰማዕቱም ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ ቢጠጣው እንደ ጨረቃ ደምቆ እንደ አበባ አሸብርቆ ተገኝቷል፤ ጠንቋዩ ማረኝ ብሎ ከእግሩ ሥር ወደቀ፡፡ ንጉሱም ጊዮርጊስን በመንኰራኩር አስፈጭቶ ትልቅ ጉድጓድ ውስጥ ዘግቶ አትሞበት ሄደ፡፡ ጌታችንም የተፈጨውን የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋ በእጁ ዳስሶ ፈውሶታል፡፡ ወደ ንጉሥም ተመልሶ “አምላኬ ከሞት አዳነኝ” በማለት መሰከረ፡፡

በፊቱም ሙት ማስነሳትና በርካታ ድንቅ ተአምራት አድርጎ ቢያሳየውም አላመነም ይልቁንም በተደጋጋሚ አሰቃው ጌታችንም ሦስት ጊዜ ከሞት አስነሣው፡፡ በመጨረሻም ሚያዝያ 23 ወታደሮች ሥጋውን ፈጭተው በደብረ ይድራስ ተራራ በትነውት ወደ ንጉሡ ሲመለሱ በመንገድ ከኋላቸው ሄዶ “አምላኬ ከሞት አዳነኝ” ሲላቸው በጌታችን አምነው በመመስከርም በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስም በሰይፍ አንገቱን ተመቶ ሲሞት ሰባውን ነገስታት አጥፍቷቸዋል፡፡ ስለ ክርሳቶስ ፍቅር ሲሉ ዓለምን የናቁ ገዳማውያን ይህን አብነት አድርገው ይጸናሉና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡  
 

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




በወሎ አካባቢዎች የተማሪዎች እና መምህራን ስደት በከፍተኛ መጠን ጨመረ ተባለ‼️

በሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች የተማሪዎች እና የመምህራን ስደት እየጨመረ ነው። በአንዳንድ ወረዳዎች ወላጆች ልጆቻቸውን እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ብቻ በማስተማር ወደ አረብ ሀገራት ይልካሉ። በ2017 ከሐብሩ ወረዳ ብቻ ወደ 52 መምህራን ሥራ መልቀቃቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

ትምህርታቸውን እያቋረጡ ወደ አረብ አገር በስደት ከሚሄዱ ተማሪዎች በተጨማሪ መምህራን የስደቱ አንድ አካል መሆናቸውን የባቲ እና ተሁለደሬ ወረዳ የትምህርት ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

‹‹መምህራን ራሱ የስደቱ አንድ ሰለባ ሆነዋል፡፡ ከመምህራንም ግማሹ በህጋዊ መንገድ በህገወጥ መንገድም የሚሄዱ አሉ፡፡ ከአንድ ትምህርት ቤት ምሳሌ ለማንሳት ሰባት(7) መምህራን ለቀዋል፡፡

ባቲ ወረዳ ኤላ ትምህርት ቤት፡፡››
በተመሳሳይም በሰሜን ወሎ ሀብሩ ወረዳ የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ኮሪደር በመሆኑ በአካባቢው የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርት አቋርጠው ስደትን ምርጫ ቢያደርጉም የመምህራን ስራ አቋርጦ መጓዝ ግን አስደንጋጭ መሆኑን የወረዳው የሀብሩ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መንግስቱ ደረጀ ይናገራሉ፡፡

‹‹የማቋረጥ ምጣኔው የተማሪዎች ብቻ ሳይሆን መምህራን በዘንድሮው አመት ላይ ወደ 52 መምህራን ለቀዋል፡፡ ግማሹ አረብ ሀገር የሄደ አለ፤ ግማሹ ሌላ ስራ ይዟል፤ የሚሄዱት ግን ተማሪዎች ፍልሰት ባለበት ህገወጥ የሰዎች ዝውውር በሚከወንበት አካባቢ ያሉት ናቸው፡፡››
በስደት ወደአረብ ሀገር በሚደረግ ጉዞ ምክንያት የትምህርት ዘርፉ ችግር እያጋጠመው ነው የሚሉት የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መመሪያ ሃላፊ አቶ አለምነው አበራ ማህበረሰቡ ለስደት ያለው የተሳሳተ አመለካከት ፈተና ሆኗል ይላሉ፡፡

‹‹ አሁን ተሁለደሬ ወረዳ በረሃ ውስጥ አንድ ትም/ቤት አለ እነርሱ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት እስከ 8ኛ ክፍል ብቻ ነው፡፡

የ8ኛ ክፍል መልቀቂያን ካርድ እስከሚይዙ ማለት ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ልጆቻቸውን ወደ አረብ ሀገር ልከው የማን ነው ልጅ ብር ይዞ የመጣ ነው እንጂ ማን አስተምሮ ዶ/ር አደረገ የሚል የለም፡፡ እና በጣም የከፋ ነው፡፡ ሽፋኑን ስናየው ደግሞ በየአመቱ የ2ኛ ደረጃ እየቀነሰ ነው"ብለዋል።
(Dw)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
900,000 ብር ምን መግዛት ይችላል?

መኪና? ቤት?

በዚህ ጊዜ 900,000 ብር ምንም መግዛት አይችልም ።

እኛ ጋር ግን በ900,000 ብር ሱቅ መግዛት ትችላላችሁ ።

ያውም እስከ 200,000 ብር መከራየት የሚችል ሱቅ።

ፒያሳ አድዋ ዜሮ ዜሮ አጠገብ 20 ካሬ ሱቅ አየሸጥን ነው።

ከግራውንድ እስከ 5ኛ ፎቅ።

ለሁለት ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው።

ፈጥነው ይደውሉ!

ለበለጠ መረጃ (Direct/ Whatsapp) ፦ በ 0914054112 ይደውሉ


ህወሓት‼️

ህወሓት የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ወደ ቀያቸው ለመመለስ የነዳጅ፣የሸቀጥ እና የቱሪስት ጉዞ እገዳ ሊነሳ ይገባል ሲል መልዕክት አስተላልፏል።

የተፈናቀሉ ወገኖቻችን የኢትዮጵያ መንግስት የገባውን ውል ባለመፈጸሙ ምክንያት ወደ ቀያቸው ሊመለሱ አልቻሉም። ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ላለፉት አራት ክረምት በብርድ፣ በርሃብና በስቃይ እየተሰቃየ ያለው ህዝብ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጠው የኢትዮጵያ መንግስት፣ ተደራዳሪ አካላት እና አለም አቀፍ ማህበረሰብ በተደጋጋሚ ተማጽነዋል።

ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት በየእለቱ እየሞተ ያለውን ህዝባችንን ለመታደግ የገባውን ቃል ከመፈፀም ይልቅ በተፈናቀሉት ወገኖቻችን ላይ ሌላ የፖለቲካ ቁማር በመጫወት በአሮጌ እና አዲስ በተቀጠሩ ካድሬዎቹ አማካኝነት እየሰራ ነው"ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት ያስተላለፋቸውን የዕገዳ መሰናክሎች በአስቸኳይ በማረም የፕሪቶሪያ ስምምነትን በማክበር ስምምነቱን ለማስቀጠል አወንታዊ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል ብለን እናምናለን"ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


ባለፉት 15 ቀናት ውስጥ 32 ፖለቲካዊ ግጭቶች መከሰታቸውን ኢትዮጵያን ፒስ ኦብዘርቫቶሪ ገለፀ፡፡ ተቋሙ አዲስ ባወጣው ሪፖርት እንዳስታወቀው ይህ ግጭት ቀደም ካለው ሁለት ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በ22 ፐርሰንት ቀንሷል፡፡

ከተከሰቱት 32 ግጭቶች ውስጥ 11ዱ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ መሆናቸውን ያስረዳው ሪፖርቱ ይህም ቀደም ካለው ሁለት ሳምንት በ15 ፐርሰንት እንደቀነሰ አስረድቷል፡፡

ከሜይ 10 እስከ 23 ባሉት ቀናት በመንግስትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል 12 ውጊያዎች መከናወናቸውን መመዝገቡን ያስታወቀው ሪፖርቱ ይህም በአብዛኛው በምእራብ ጎጃም የተከናወነ መሆኑን ገልጿል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


ስምረት‼️

ስምረት ፓርቲ የመጀመሪያውን ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጥ ነው፡፡ በእነአቶ ጌታቸው ረዳ የተመሰረተውና ከምርጫ ቦርድ ቅድመ እውቅና የተሰጠው ‹‹ስምረት›› ፓርቲ የመጀመሪያውን ጋዜጣዊ መግለጫ በአዲስ አበባ እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡

ፓርቲው "ለመንግስት መገናኛ ብዙሀን" በላከው ጥሪ እንዳስታወቀው፣ መግለጫውን የሚሰጡት አቶ ጌታቸው ረዳና ሌሎችም የፓርቲው አመራሮች ናቸው፡፡ መግለጫው ግንቦት 23 ቀን በሸራተን አዲስ ሆቴል እንደሚሰጥ ለመረዳት ችለናል፡፡ ስምረት ፓርቲ በተጨማሪም በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዲገኙ በትግራይ ክልል ላሉ ሚዲያዎችን የጥሪ ደብዳቤ ልኳል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


"ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን አባቶች በከተማችን እየተከናወኑ ያሉ ግዙፍ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል ። ከጉብኝት በኋላ በፅህፈት ቤታችን ተቀብለን በተለያዩ ከተማ አቀፍ ጉዳዮች እና የጋራ ስራዎች ዙሪያ ተወያይተናል።

ብፁዓን አባቶቻችን ከለውጡ ጀምሮ በከተማችን መንግሥት ያከናወናቸውን የልማት ስራዎች በመጐብኛት ለተሰሩት ስራዎች ያላቸውን አድናቆት ገልጸው፣ በቀጣይ ጊዜያትም ፈጣሪ ክንውንን እንዲሰጠን በፀሎት እና በቡራኬ እንደማይለዩን ገልጸውልናል።

እኛም የሀገራችን ብቻ ሳይሆን የአህጉራችን መዲና እና የዓለም አቀፉ ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ መናገሻ የሆነች አዲስ አበባችንን ይበልጥ ለመለወጥ ያለንን ቁርጠኝነት እየገለጽን፣ አባቶቻችን በምክር እና ጸሎት ሁልጊዜ ከእኛ ጋር ስላሉ እና ስላበረታቱን ከልብ እናመሰግናለን።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


ከኤርትራ መንግስት በይፋ ለሚቃጣው የጠብ አጫሪ ንግግር መንግስት በሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መልኩ ምላሽ መስጠት እንዳለበት የምክር ቤት አባላት ገለጹ

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ አካባቢያዊ፤ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ህግጋትን ባከበረ መልኩ እንደምትንቀሳቀስ እና ጎረቤት ሀገራትም የሰጥቶ መቀበል መርህን የተከተለ ግንኙነት ማድረግ እንደሚገባቸው የተናገሩት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ናቸው፡፡

መንግስት በኤርትራው ፕሬዚዳንት በኩል የቀረበውን ንግግር መነሻ በማድረግ ሰጣገባ ውስጥ መግባት አይፈልግም ማለት ብሄራዊ ጥቅምን አይስጠብቅም ማለት አይደለም ብለዋል።

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሌሎች የጎረቤት ሀገራት ጋር እንደሚያደረገው ሁሉ ከኤርትራ ምክር ቤት ጋር የአቻ ግንኙነት ለማድረግ ፍላጎት ቢኖረውም በኤርትራ በኩል ምክር ቤት ባለመኖሩ ምክንያት አለመሳካቱን ሌላኛው የምክር ቤቱ አባሉ ዶክተር ፈቲህ መሃዲ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ከሰሞኑን የኢትዮጵያን የውስጥ ጉዳይ በተመለከተ ያደረጉት አሉታዊ ንግግር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የሚያሻክር ከአንድ መሪም የማይጠበቅ ነው ብለውታል፡፡

ከዚህ አይነት ንግግር ይልቅ መተማመንና አብሮነትን የሚያጎለብት፤ መቀራረብን የሚያበረታታ ንግግር ማድረግ ከፕሬዚዳንቱ ይጠበቅ እንደነበር በመግለጽ፤ ምክር ቤቱም ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ምክር ቤት ጋር የሚያደርገውን አይነት ግንኙነት ለመፈጠር ፍላጎት ቢኖረውም በኤርትራ በኩል አደረጃጀቱ ባለመኖሩ ይህን ማድረግ አልተቻለም ብለዋል፡፡

#menahriaFm

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


ቺሊ ከእስራኤል የነበራት ወታደራዊ ትብብር አቋረጠች

ቺሊ እንዳስታወቀችው፤ እስራኤል በፍልስጤም ላይ በጋዛ እያደረሰች ባለችው ቀውስ ምክንያት የመከላከያና የአየር ሃይል የጋራ ስራዎችን አቋርጣለች፡፡

ይሄ የቺሊ ውሳኔ በእስራኤልና በሃገሪቱ ቀድሞም ይስተዋሉ የነበሩ የሃሳብ ልዩነቶችን ያሰፋዋል ተብለዋል፡፡

ቺሊ 2023 ላይ እስራኤል በመጠለያ ጣቢያዎች ላይ የፈጸመችውን ጥቃ ተከትሎ ደቡብ አፍሪካ ባለማቀፉ ፍርድ ቤት በእስራኤል ላይ የከፈተችውን ክስ እንደምትደግፍ ገልጻለች፡፡

የሁለቱ ሃገራት ፖለቲካዊ ውጥረት ይበልጥ እንደጨመረ ተገልጿል፡፡

የቺሊ መንግስት እስራኤል በጋዛ ያላትን እንቅስቃሴ የተቃወመ ሲሆን ሃገሪቱ አለማቀፍ ህጎችን በማክበር የሰብአዊ እርዳታዎች እንዲገቡ መፍቀድ አለባት ስለማለቱ የዘገበው ፕረስ ቲቪ ነው፡፡


ግንቦት 22 ሁለት ታላላቅ ሐዋርያት፣ ከ72ቱ አርድእት ውስጥ አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ እንድራኒቆስ ዐረፈ፡፡

ዳግመኛም በማግሥቱ ሐዋርያው ቅዱስ እንድራኒቆስን ገንዞ የቀበረውና ወዳጁ የሆነ ሌላኛው ሐዋርያ ቅዱስ ዮልዮስ ዐረፈ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ እንድራኒቆስን የክብር ባለቤት ጌታችን ነው የመረጠው፡፡ እርሱም የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዲሰብኩ ጌታችን ከመከራው በፊት ከላካቸው ከ72ቱ አርድእት ውስጥ የተቆጠረ ነው፡፡

በጽርሐ ጽዮንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከከበሩ ሐዋርያት ጋራ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብሎ የከበረች ወንጌልን በብዙ ሀገራት ሰብኳል፡፡ በሔደባቸው አካባባዎችም ቅዱስ ወንጌልን ሰብኮና አስተምሮ በማሳመን በርካቶችን አጥምቋል፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት በኑቢያ ሀገር ላይ ኤጲስቆጶስ አድርገው በአብሮተ እድ ሾሙት፡፡

በኑቢያም የከበረች ወንጌልን በሰበከ ጊዜ በጨለማ ባለማወቅ ውስጥ የሚኖሩ ብዙ አረማውያንን የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደጌታችን ሃይማኖት አስገባቸው፡፡ በኋላም ከሐዋርያው ዮልዮስ ጋር በአንድነት በብዙ ሀገራት ዞረው በማስተማር አልጫውን ዓለም በወንጌል ጨውነት አጣፍጠውታል፡፡ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማየ ዮርዳኖስ ሃብተ ወልድና ስመ ክርስትና እንዲያገኙ አጥምቀዋል፡፡ ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት፣ ህሙማነ ስጋን በድንቅ ተአምራት ፈውሰዋል፤ አጋንንትን አስወጥተዋል፤ ሙታንንም አስነሥተዋል፡፡ የጣዖታት ቤቶችን አፍርሰው በምትካቸው በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ እንድራኒቆስና ወዳጁ  ሐዋርያው ቅዱስ ዮልዮስ አገልግሎታቸውን በፈጸሙ ጊዜ ጌታችን ከድካም ወደ ዕረፍት ከኀዘንም ወደ ደስታ ሊወስዳቸው ወደደ፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ እንድራኒቆስ በስጋ ህመም ተያዘና ግንቦት 22 ቀን ዐረፈ፡፡ ወዳጁና የአገልግሎት አጋሩ ቅዱስ ዮልዮስም በታላቅ ሐዘን በክብር ገንዞ ከቀበረው በኋላ ከእርሱ እንዳይለይ ጌታችንን አጥብቆ ለመነው፡፡ የፍቅር የሆነች ፍጹም ጸሎቱ ተሰምታ ዮልዮስም በቀጣዩ ቀን ዐረፈ፡፡ ቅዱስ ዮልዮስ ትውልዱ ከይሁዳ ነገድ ከእስራኤል ልጆች ወገን ነው፡፡ ጌታችን ከጠራቸው 72ቱ አርድእት ውስጥ አንዱ ሆኖ ተመርጦ ከሐዋርያት ጋር የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከተቀበለ በኋላ የከበረች ወንጌልን ዞሮ ሲሰብክ ታላቅ መከራ ተቀብሏል፡፡ የከበሩ ሐዋርያትም በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሾመውት ከቅዱስ እንድራኒቆስ ጋር በተለያዩ አገሮች ውስጥ የከበረች ወንጌልን እንዲሰብክ ላኩት፡፡ ቅዱስ እንድራኒቆስም ከአንድ ቀን በፊት ባረፈ ጊዜ ይህ ቅዱስ ዮልዮስ ገንዞ በክብር ቀበረው፡፡

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ዮልዮስ ከጓደኛው ከቅዱስ እንድራኒቆስ እንዳይለይ ጌታችንን በጸሎት ቢጠይቀው ጌታችንም ፈቃዱን ፈጸመለትና በማግሥቱ ዐረፈ፡፡ የከበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስም እነዚህን የከበሩ ሐዋርያት ለሮሜ ክርስቲያኖች በጻፈው መልዕክቱ “እንድራኒቆስንና ዮልዮስን ሰላም በሏቸው” ሲል ስማቸውን ያነሳል፡፡ ጌታችን በጠራቸው ጊዜ ያላቸውን ሁሉ ትተው የተከተሉት ቅዱሳን ሐዋርያት የዓለምን መከራ ተቋቁመው በአህዛብ መሐል ተመላልሰው የወንጌልን ብርሃን በምድር ሁሉ አብርተዋል፡፡ በዘመናችንም ዓለምን ንቀው የመነኑ ገዳማውያን ለጌታችን ባላቸው ፍቅር ሌሊትና ቀን ራሳቸውን ለእርሱ እያስገዙ በጾምና በጸሎት ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡ የከበሩ ሐዋርያት ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Показано 20 последних публикаций.
OSZAR »